ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርን አሰናበቱ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ዛሬ አሰናብተዋል።

አምባሳደር ጊታ ፓሲ የሹመት ደብዳቤያቸውን ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረባቸው እንደሚታወስ ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።