ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዩኤን ኤይድስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን ጋር ተወያዩ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ላይ የሚሰራውን የተ.መ.ድ አካል (UNAIDS) ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ እና የዩኤን ኤድስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን በኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በተያዙ ዕቅዶች ላይ መምከራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡