ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

ፕሬዝዳንቷ ድጋፉን ያደረጉት በመዲናዋ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ለሚኖሩ 300 ለሚሆኑ ወገኖች መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳት ረገድ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በችግር ውስጥ የሚገኙና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ከዚህ አኳያ በክፍለ ከተማው ዛሬ ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ሴቶችና ወጣቶችን በዘላቂነት የሚደግፍ ፕሮጀክት እየተተገበረ ስለመሆኑም ለአብነት ማንሳታቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW