ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የእንኳን ደስ አለን መልእክት አስተላለፉ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

የካቲት 13/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኅዳሴው ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን በማስመልከት የእንኳን ደስ አለን መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቷ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት “በንጉሡ ራዕይ ተጀመረ፣ ድፍረት ተከተለ፣ አስቀጣዮች መጡ፣ ግድባችን ኃይል አመነጨ! እንኳን ደስ አለን!” ብለዋል።

“ሃሩርን ተጋፍጦ፣ ጤናውን እና ሕይወቱን ሠውቶ፣ የአገርን ጥቅም የሙጢኝ ይዞ ተደራድሮ፣ ካለው አካፍሎ፣ አገሬ ብሎ ለተነሣ ሁሉ ቀኑ የእናንተ ነው፣ እጅ እነሳለሁ” ሲሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።