ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

                           ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌህ
ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት ለመመስረት የሚያስችልዎትን ድምጽ በማግኘትዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡
በመልዕክታቸውም “በእርስዎ መሪነት ወዳጅ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ጊዜ የሚበለጽግና ዘመናዊ ዕሴቶችን የሚቀበል ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ለዓለም እያሳየ ይገኛል” ይገኛል ማለታቸውን ከጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡