95 የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ለአራት ተከታታይ ቀናት በጉጂና በቦረና ዞኖች ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ባደረገው ኦፕሬሽን 95 የሸኔ ተጣቂዎችን ሲደመስስ፤ በርካቶች መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኦፕሬሽኑ የሸኔ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበረው ብዛት ያላቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ነው የተባለው።

የሸኔ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበሩ ሞተር ሳይክሎች እና የተለያዩ ቁሳቁስ መያዝ መቻሉንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ድሉ እንዲመጣ የሰላም ባለቤት የሆነው ህዝብ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡