ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ምክክር አካሄዱ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ጋር ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የንግድ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሄዱ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀማል አብዱላህ ጋር በአገሮቹ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ተወያይተዋል።
በነበራቸው ቆይታም ኢትዮጵያና ሳዑዲ በንግዱ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክሩባቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሁለቱ አገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነት በሚጠናከሩበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ ባለፉት አምስት ዓመታት 577 ሚሊየን ዶላር የንግድ ግብይት ማካሄዳቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።