አቶ ደመቀ መኮንን ከሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ

ሰኔ 16/2013 (ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምክራቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡