በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ሴቶች ድጋፍ እየተደረገ ነው

ሰኔ 16/2013(ዋልታ) – በትግራይ ክልል ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ለችግር ለተጋለጡ ሴቶች የህክምና እና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጹ።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቃል አቀባይ ዶክተር አደዳ ሃይለስላሰ እንደተናገሩት፤ ድጋፉ እየተደረገ ያለው በመንግስት ነው፤ በዚህም ቁጥራቸው ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
እነዚህ ወገኖች በአሁኑ ወቅት በስድስት ጤና ማዕከላት የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከህክምናው በተጨማሪ የስነ ልቦና፣ የህግ አገልግሎት ፣ የሙያ ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ዶክተር አደዳ አስታውቀዋል።
አሁን ላይ በአነስተኛ የስራ ዘርፍ ለማሰማራት የሚያግዛቸው በነፍስ ወከፍ ከ5 እስከ 10ሺህ ብር የመነሻ ገንዘብ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተጎጂዎቹን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቀሴ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲያግዙ ዶክተር አደዳ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።