የኢትዮጵያ ሴቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃግብር በአማራ ክልል አዊ ዞን ተጀመረ

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ሴቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃግብር በአማራ ክልል አዊ ዞን ተጀመረ።

ኢትዮጵያ ሴቶች ሊግ በአማራ ክልል አዊ ዞን ለአቅመ ደካሞችና ለተቸገሩ ወገኖች ቤት በማደስ መርኃግብሩን አስጀምሯል።

የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ መሠረት መስቀሌ የበጎ ፈቃድ መርኃግብሩ በመላው ኢትዮጵያ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

(በዙፋን አምባቸው)