103 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ታርሶ ለዘር መዘጋጀቱን ኦሮሚያ ልዩ ዞን አስታወቀ

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – በዘንድሮ የክረምት እርሻ 103 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ታርሶ ለዘር መዘጋጀቱን ኦሮሚያ ልዩ ዞን አስታውቋል።

በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በዘንድሮ የክረምት እርሻ 103 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ታርሶ ለዘር የተዘጋጀ ሲሆን፣ እስካሁን ከ15 ሺህ በላይ ሄክታ  መሬት በዘር ተሸፍኗል ተብሏል።

የኦሮሚያ ልዩ ዞን የግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ ጫላ አደሬ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በዞኑ የመሬት ልየታ በማድረግ ከ9 ሺህ በላይ ክላስተሮች በክረምት እርሻ በኩታ ገጠም እንዲያርሱ መደራጀታቸውን ገልፀዋል።

በሱሉልታ ወረዳ ብቻ ከ14 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በክላስተር የታረሰ ሲሆን፣ ከ10 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል።

(በደረሰ አማረ)