ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን መርቀው ከፈቱ

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ

ሰኔ 19/2013 (ዋልታ) – በአዲስ መልክ የተዋቀረውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ መርኃግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው አካዳሚውን በይፋ መርቀው ሪቫን ቆርጠዋል::

በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው አካዳሚው 722 ሚሊየን ብር በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፣ ቀሪው ገንዘብ ከቻይና ህዝብ እና መንግስት ድጋፍ የተገነባ ነው ተብሏል።

አካዳሚው እጅግ ዘመናዊ የሆነ እና ሁሉን አካታች ያደረገ፣ 600 ሰው በአንድ ጊዜ መያዝ የሚችል አዳራሽ ያለው እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ 150 ባለ አምስት ኮከብ ማረፊያ ወይም መኝታ ክፍል ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

(በሜሮን መስፍን)