የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ መንገደኞችን በማጓጓዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ መንገደኞችን በማጓጓዝ ከአፍሪካ የአንደኝነት ደረጃን መያዙ ተገለጸ፡፡

በአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2020 መንገደኞችን በማጓጓዝ የአንደኝነት ደረጃ መያዙን አፍሪካን አየር መንገድ ማህበር ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው አየር መንገዱ በ2020 አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊየን መንገደኞችን አስተናግዷል፡፡