የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኸር እርሻ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እያከናወነ ነው

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኸር እርሻ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር “ምግባችን ከደጃችን” በሚል መሪ ሀሳብ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 እየተከናወነ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ ለየክፍለከተሞች የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ግብዓት እና የቴክኖሎጂ ድጋፍም አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ የእርሻ ትራክተር፣ የአትክልት ውሃ ማጠጫ ጎማ፣ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘርም ለክፍለከተማ ተወካዮች አስረክበዋል።

በተጨማሪም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በራሳቸው ባሰባሰቡት ድጋፍ ለሴት አርሶ አደሮች የጄኔሬተር ድጋፍ አድርገዋል።

(በትዕግስት ዘላለም)