የሰላም ሚኒስትሯ በሀረር ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ


ሐምሌ 02 /2013 (ዋልታ) –
የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በሀረር ከተማ ተገኝተው ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ሚኒስትሯ ከሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላ እንዲሁም ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በከተማው በተለምዶ ሀማሬሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
በስነ-ስርአቱ ላይ የሰላም ቤተሰቦች አማካሪ ምክር ቤትና የሰላም አምባሳደሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።