ጁንታው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የጀመረውን ጦርነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በሎጊያ የሟገኙ የትግራይ ተወላጆች ገለፁ


ሐምሌ 11/2013(ዋልታ) – በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የህወሃት ቡድን በአፋር ህዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የጀመረውን ጦርነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በአፋር ሎጊያ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ።
የሽብር ቡድኑን እኩይ ተግባር በመቃወም ሰልፍ የወጡት በሎጊያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች “ጁንታው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የጀመረውን ጦርነት አጥብቀን” እንቃወማለን ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ሰልፈኞቹ ጁንታው በንፁሀን የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ የከፈተው ጦርነት በምንም አይነት መልኩ ተቀባይነት የሌለውና ሊኮነን የሚገባ አረመኔያዊ ተግባር በመሆኑ ለማውገዝ አደባባይ መውጣታቸውን ሰልፈኞቹ መግለጻቸውን ከአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የህወኃት የሽብር ቡድን በትናንትናው ዕለት በፈንቲ ረሱ ያሎ ወረዳ በኩል ጥቃት መክፈቱ ይታወሳል::