ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ

ነሃሴ 14/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መላው የኢትዮጵያ  ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፉን በተግባር በማሳየቱ ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በመላው ሀገራችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ድጋፋቸውን በተግባር በማሳየት፣ ይህቺን ድል አድራጊ ሀገር ለመጠበቅ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት በአንድነት ለቆሙ የኢትዮጵያ ጠባቂዎች ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ”  ብለዋል።