ዩኒሴፍ ለተፈናቃይ ዜጎች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ

ነሀሴ 25/2013 (ዋልታ) – ዩኒሴፍ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ዩኒሴፍ ለአማራ ክልል ለችግር ጊዜ ደራሽ በመሆኑ አመስግነዋል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይም ድጋፉን እንዲቀጥል የጠየቁት ርዕሰ-መስተዳድሩ ሌሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ለተማሪዎች ደብተር እና ስኪርቢቶ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንዲሁም ፍራሾች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ኢብኮ ነው የዘገበው፡፡
የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር በሰሜን ጎንደርና አካባቢው ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልፀው በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡
ታዳጊዎች በመጭው የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታ ለመታደም አሳሳቢ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡