ወጋገን ባንክ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የ500 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረገ

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ወጋገን ባንክ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የ500 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ባንኩ በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ለተመሰረተውና የፊስቱላ ታማሚ እናቶችና ወጣት ሴቶች ህክምና አገልግሎት ለሚሰጠው ማዕከል ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ድጋፍ ስለማድረጉ የባንኩ ‹የብራንች ባንኪንግ› ምክትል ፕሬዝዳንት ክንዴ አበበ ገልፀዋል፡፡
ድጋፉ ለ11 የፊስቱላ ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት እንደሚውል ደግሞ የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተስፋዬ ማሞ አስታውቀዋል፡፡
(በአመለወርቅ መኳንንት)