ባንኮች ከትርፋቸው የሚያስቀምጡት የመጠባበቂያ መጠን ከፍ እንዲል መወሰን

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ከነገ ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱትን የመጠባበቂያ መጠን ከ5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች መጠባበቂያ እና የብሔራዊ ባንክ ማበደሪያ ወለድ ምጣኔን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም ከነገ ነሐሴ 26/2013 ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በብሄራዊ ባንኩ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱት የመጠባበቂያ መጠን ከነበረበት 5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡
ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 ከፍ እንዲል መደረጉም መግለጫው አመልክቷል፡፡