መስከረም 24 የመንግሥት ምስረታ ይካሄዳል

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – በመጪው መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም 6ኛው ዙር የመንግሥት ምስረታ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።
ሰኔ 14 ቀን 2013 በተደረገው 6ኛ ዙር አገር ዐቀፍ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ እንዳገኘ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ውጤቱን ተከትሎ ፓርቲያቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደየተሳትፏቸው መጠን በአስፈፃሚው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለማካተት ጥረት እንደሚደረግ ቃል መግባታቸውም የሚታወስ ነው፡፡