የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት

መስከረም 11/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሂደው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሰ ስርጭት አጠናቀቀ፡፡

ቦርዱ በሐረሪ ክልል፣ በሶማሌ ክልል እና በደቡብ ክልል ለሚያካሂደው ምርጫና ሕዝበ ውሣኔ፤ ለድምፅ መስጫና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁስን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች አሰራጭቶ ማጠናቁን ነው የገለጸው፡፡

ከቦርዱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በአዲስ አበባና ቅርብ አካባቢዎች ለሐረሪ ተወላጆች ለተከፈቱት ምርጫ ጣቢያዎች የሚሠራጩትን የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረስ ያለበትን የጊዜ እርዝማኔ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!