የአፍሪካ ሕብረት ጥላቻ ንግግርን የመካላከል ዘመቻ

መስከረም 11/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ሕብረት “ለጥላቻ ንግግር ቦታ የለም” በሚል መሪ ቃል የጥላቻ ንግግርን ለመካላከል ያለመ ዘመቻ ይፋ አደረገ።

የሕብረቱ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ከምሥራቅ አፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ ድርጅት ጋር በመሆን የአለም የሰላም ቀንን በታንዛንያ አክብሯል።

በዚህ ወቅት በሕብረቱ ወጣት የሰላም አምባሳደሮች የሚመራ “ለጥላቻ ንግግር ቦታ የለም” የሚል ዘመቻ ይፋ አድርጓል።

ዘመቻው በማኅበራዊ የትሰስር ገጾች ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ግለሰቦች የሚመራ ሲሆን፣ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከጥላቻ ነጻ የሆነ ውይይትን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የጥላቻ ንግግር አስከፊነት እና የሚያመጣውን መዘዝ በተመለከተ ዘመቻው ትምህርት እንደሚሰጥ ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!