የጠ/ሚ ዐቢይ መልዕክት ለሱዳን ህዝብ

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወቅታዊ ችግር ሱዳናዊያን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሳቸው እንደሚፈቱት እናምናለን ሲሉ ገለጹ።

ለሱዳን ህዝብ ያለንን ድጋፍ በሙሉ ልብ እናረጋግጣለን ሲሉም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሱዳን በአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያና ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ የሚያርጉት ሽግግር በርካታ ተግዳሮቶች እየገጠሙት ነው ሲሉ በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስትም ሱዳን የገጠማትን ወቅታዊ ችግር በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነም ገልጸዋል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!