የእሌኒ ገብረመድህን (ዶ/ር) የተመድ ሹመት

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) የቀድሞ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ኢሴክስ) መስራች እሌኒ ገብረመድህን (ዶ/ር) የተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ) የአፍሪካ ዋና የፈጠራ ስራ ኃላፊ በመሆን ተሾሙ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅትን (ኢ.ሲ.ኤክስ) እንዲሁም ብሉ ሙን የተሰኙ ተቋማትን በመመስረት እና በመምራት የሚታወቁት እሌኒ (ዶ/ር) ለዚህ አዲስ ስራቸው ወደ ኒውዮርክ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ የወጣቶች የፋይናንስ ፈጠራ አብዮት ቲምቡኮትን በማስጀመር ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወቱ ዩኤንዲፒ በድረ ገጹ ማስነበቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካን የወደ ፊት ዕጣ ፈንታ፣ ዲጂታላይዜሽንን ማሳደግ እና ወጣቶችን ማበረታታት ትኩረት አድርገው ይሰራሉ ብዬ አምናለሁ ሲሉም የተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ጸሐፊ እና የዩ.ኤን.ዲ.ፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁንና ኢዚያኮንዋ ገልጸዋል፡፡