ከዓለም ዐቀፍ የሰብኣዊ እርዳታ አቅራቢዎች ጋር ውይይት

የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭት ሂደት ላይ ከአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭትና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በአማራ እና አፋር ክልል የእርዳታ ስርጭት ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ለማድረስ የየዕለት ግብ የተያዘ ቢሆንም፤ ወደ ክልሉ ገብተው ባልተመለሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምክንያት ሂደቱ መስተጓጎሉ ይታወሳል፡፡

በዚህም ተሽከርካሪዎቹን በማስመለስ ረገድ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጭና አቅራቢ ድርጅቶቹ ኃላፊነት ወስደው ተገቢውን አመራር በመስጠት መመለሳቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው መግባባት ላይ ተደርሷል::