6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀረሪ

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀረሪ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) ማልደን በመነሣት ለአምስት ዓመት የሚያስተዳድረንን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጠናል ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የሐረር ከተማ መራጮች ተናገሩ።

መራጮቹ ድምጽ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ምርጫው ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ እየተካሄደ የሚገኘው ምርጫ ቀደም ባሉ ጊዜያት ከተካሄዱ ምርጫዎች ጋር ሲነጻጸርም የተሻለ እና ህዝቡም በራሱ ፈቃድ ያሻውን የመረጠበት መሆኑን አሰተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱም አንድም ጣልቃ የሚገባ ሰው የለም ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በነጻነት ለሚፈልጉት ፖርቲና ግለሰብ ድምጽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

በምርጫ ሂደት እንደዚህ ያለ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ ከዚህ ቀደም አይተው እንደማያውቁም አስረድተዋል። የምርጫው ሂደትም ሠላማዊ መሆኑን ለኢዜአ በሰጡት አስተያየታቸው ጠቁመዋል።

በሐረሪ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን 229 የምርጫ ጣቢያዎችም አሉ።

በዛሬው ዕለትም ከ147 ሺሕ በላይ ሰዎች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።