ትምህርት ሚኒስቴር 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) – የትምህርት ሚኒስቴር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርቤቶች ድጋፍ የሚሆን 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርቤቶች ድጋፍ የሚሆን 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ለወደሙ ትምህርት ቤቶች 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን አስታወቀዋል።

የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በክልሉ በአሸባሪው ህወሃትና ተላላኪዎቹ የተቀነባበረ አገር የማፍረስ ተልእኮ በርካታ የመንግስት፣ የህዝብና የግለሰብ ተቋማትና ንብረቶች ውድመት እንደደረሰባቸው ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ የወደሙ ተቋማትን መልሶ የመገንባት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በዙፋን አምባቸው