የሽብር ቡድኑን ፕሮፖጋንዳ በትምህርት ዘርፉ እክል እንዳይፈጥር ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

ኅዳር 10/2014 (ዋልታ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ በትምህርት ዘርፍ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ያካተተ ውይይት እየተደረገ ነው።
የጥፋት ቡድኑ እኩይ አላማ እንዳይሳካና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ኢንዲቀጥል በትምህርት ቤቶች መምህራን እና ተማሪዎች በማደራጀት ከውስጥና ከውጭ ሰርጎ ገቦች አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባም በውይይቱ ተመላክቷል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ መዝገበ ይስማው እንዳሉት አገራችን በአሁኑ ወቅት በአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ የተጋረጠባትን የኅልውና ዘመቻ ለመመከት በሚደረገው ጥረት የትምህርቱ ዘርፍ ማኅበረሰብ እና በትምህርት ቤቶችን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ወሳኝ ነው፡፡
በቀጣይ የሽብር ቡድኑ የመማር ማስተማሩን ሥራ በቅጥረኞቹ ፕሮፖጋንዳ እንዳያስተጓጎል የትምህርት ዘርፍ ተዋንያን የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
በሙባረክ ፋንታው