ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) የሰላም ሚኒስቴር በአገሪቱ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎችን በቀጣይነት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከጀርመን ኮፕሬሽን (GIZ) ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ስራዎቹ ላለፉት ሶስት ዓመታት እየተከናወኑ የነበሩና በሁለቱም ወገን አስፈላጊነታቸው በመታመኑ እንዲቀጥሉ ስምምነት ላይ በመደረሱ ነው ተብሏል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ እና የGIZ የኢትዮጵያና ጅቡቲ ተወካይ ፒተር ፓለሽ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው የጀርመን መንግስት በGIZ በኩል እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናውን ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡