“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” ኢትዮጵያዊነት አይበገሬነት መሆኑን ያሳየ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኅዳር 29/2021 (ዋልታ) – በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እየተመራ ድል የተቀናጀው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ኢትዮጵያዊነት አይበገሬነት መሆኑን ያሳየ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ድሉ የውጭ ኃያላን የተባሉትን ጭምር ያሸበረ ነው ያሉት ከንቲባዋ አንድነታችንና ርብርባችን በቀጣይ የልማት ስራዎቻችን ላይ ሊደገሙ ይገባል ብለዋል።
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ከንቲባዋ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም የገጠማት ፈተና የመኖርና ያለመኖር ብሎም ታሪክን የማስቀጠል ብርቱ ትግል ነበር ነው ያሉት።
በዚህ የአርነት ትግል ውስጥ በሽብር ቡድኑ የተሰው ወገኖች ለሀገር የከፈሉት መስዋእትነት ነው ያሉት ከንቲባዋ ሁሉም ዜጋ በተለያዩ የዘመቻው ግንባር ዘርፎች የተሳተፉበት መሆኑንም አውስተዋል።
ከጦር ግንባር ተጋድሎ ባሻገርም በምጣኔ ኃብቱ የዘመቻ ግንባር የሽብር ቡድኑ የሸረባቸውን የኢኮኖሚ አሻጥሮች መቆጣጠር ላይ ጥብቅ ሥራዎች ስለመሰራታቸው ከንቲባ አዳነች አብራርተዋል።
የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ከውጭ ኃይሎች ጋር ተመሳጥሮ በኢትዮጵያ ላይ የደቀኑት የህልውና አደጋ ተቀልብሷል ያሉት ከንቲባ አዳነች የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬም እንደጥንቱ አይበገሬነቱን በውጭ ኃያላን ተብዬውች ላይም መድገሙን አውስተዋል። ይህን አይበገሬነቱን፣ ታታሪነቱንና አንድነቱን በስራና ልማቱ ላይ ሊደግም ይገባዋል ብለዋል።
በደምሰው በነበሩ