የሲዳማ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ

ኅዳር 29/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልል መስተደድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ በትናንትናው ዕለት በጀመረው ሰብሰባው በሶስት አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በማፅደቅ ተጠናቋል።
በዚህም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከተሞችን እንደገና ለማቋቋምና ለማደራጀት፣ ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ የመስተዳድር ምክር ቤቱ በጥልቀት ከተወያየ በኃላ መስተካከል ያለባቸው አስፈላጊ ማስተካከያ ተደርጎ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በተጨማሪም በቀረበው ለኢንቨስትመንት ተግባር የሚውል የገጠር መሬትን በሚመለከት ረቂቅ ደንብ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡