ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የአዳሚ ቱሉን የእርሻ ማዕከል ጎበኙ

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የአዳሚ ቱሉን የእርሻ ማዕከል ጎበኙ።

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ቡድን በምስራቅ ሸዋ በአዳሚ ቱሉ የሚገኘውን የግብርና ጥናት እና ምርምር ማዕከል የሚገኘውን ባዮ ቴክኖሎጂ ክፍል ጎበኝቷል። ማዕከሉ በኦሮሚያ ክልል አንድ ቦታ ብቻ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

በመቀጠልም በአዳሚ ቱሉ የሚገኘውን በመስኖ ቴክኖሎጂ ታግዞ የተሰራው ፕሮጀከት አሰመርቋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ28 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባና 57 ሄክታር መሬትን ያረፈ መሆኑ ተጠቁሟል።

በመቀጠልም በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ቡድን በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የላሞች መራቢያ አስመርቋል።

በእመቤት ንጉሴ