ብልፅግና ፓርቲ ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) ብልፅግና ፓርቲ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ 200 ዘማች ቤተሰቦች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ለአገር ኅልውና በግንባር እየተዋደቁ ለሚገኙት ዘማቾች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የዘመቻ ቤተሰብን ሰብል በመሰብሰብ እንዲሁም በዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸውን ቁስለኞችን በመጠየቅ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።

በሚኪያስ ምትኩ