ቦርዱ ከፖለቲካ ፖርቲ አመራሮች ጋር ምክክር እያካሄደ ነው

ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፖርቲ አመራሮች ጋር በሚያደርገው ምክክር ከፓርቲ ተወካዮች ጋር በዛሬው እለት መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ለመወሰን የወጣ መመሪያን ይገመግማል ተብሏል።

በሀገሪቱ በፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ እየደረሰ ስላለው እንግልትና እስርም ውይይት የሚያካሄድ ይሆናል ተብሏል።

እንደ ኢብኮ ዘገባ ቦርዱ በፓርቲዎች መካከል የሚደረገውን ቋሚ ውይይት ሰነድ ለማሻሻል የቀረበውን የማሻሻያ ሰነድ አቅርቦ መግባባት ላይ ለመድረስ እንደሚሰራም ነው የተገለፀው።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከዚህ ቀደም በፓርቲ አመራሮች ላይ የደረሰን እስር እና መንገላታት የሚያጣራ ቡድን ወደ ክልል ከተሞችና ወረዳዎች መላካቸውን ተናግረዋል።