በተባበሩት መንግሥታት የሚሰሩ አንዳንድ ግለሰቦች የግል አጀንዳቸውን በማራመድ ሕግን እየጣሱ መሆኑ ተገለፀ

ቾይስ ዑፎኦማ ኦኮሮ

ጥር 8/2014 (ዋልታ) በተባበሩት መንግሥታት የሚሰሩ አንዳንድ ግለሰቦች የግል አጀንዳቸውን በማራመድ የተቋሙን ሕግጋትና እሴት እየሸረሸሩ ነው ሲሉ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የፓኪስታን ሰብኣዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (ኦቻ) ኃላፊ ቾይስ ዑፎኦማ ኦኮሮ ገለፁ።

ተቋሙ የአገራትን ሉኣላዊነት ባከበረ መልኩ ሰላምን ለማምጣት የሚሰራ ዓለም ዐቀፍ ተቋም ቢሆንም በአንዳንድ ግለሰቦች ያልተገባ እንቅስቃሴ እየተስተዋለበት መጥቷል ብለዋል።

ኃላፊዋ ቾይስ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ መንግሥታቱ የአገራትን ሉኣላዊነት አክብሮ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው የትሕነግ ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ከ2 ሺሕ በላይ የጤና ተቋማትን ሲዘርፍና ሲያወድም የዓለም ጤና ድርጅትን የሚመራው የትሕነጉ ቴድሮስ አድሐኖም ዝምታን ከመምረጥ ይባስ ብሎ ከአሸባሪው ጎን በመሰለፍ ስለአገሪቱ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨ ነው፡፡

ቾይስ ታዲያ “ምን አልባትም በመንግሥታቱ የሚሰሩ አንዳንድ ግለሰቦች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያልተገባ ነገር ሊሰሩ ይችላሉ፤ ያ ግን የተባበሩት መንግሥታት ሚና አይደለም” ይላሉ።