በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት የማሊ ፕሬዝዳንት አረፉ

ጥር 8/2014 (ዋልታ) በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት የማሊ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባክር ኬይታ ህይወታቸው አለፈ፡፡

በ76 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከመስከረም 2006 ጀምረው በመፈንቅለ መንግሥት እስከተወገዱበት የዛሬ 1 ዓመት ተኩል ወይም ነሐሴ 2012 ድረስ ማሊን በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡

የማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አበዶላዬ ዲኦፕ በቲውተር ገጻቸው ‹‹የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬይታ ህልፈትን መስማት በጣም ያሳዝናል›› ሲሉ ነው ህይወታቸው ማለፉን ያሳወቁት፡፡

የህልፈታቸው ምክንያት ግልፅ ባይደረግም ባማኮ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንዳረፉ ነው የተገለጸው፡፡