ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅግጅጋ ከተማ የተገነቡ የአስፓልት መንገዶችን ጎብኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥር 17/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅግጅጋ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ባለፉት ሶስት ዓመታት የተገነቡ የአስፓልት መንገዶችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ ከሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ለአገልግሎት የበቁት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ የ05 ቀበሌ፣ የዱአሌ እንዲሁም የሼክ ኑር ኢሴና የአየር ደጋ የአስፓልት መንገዶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሌ ክልል የነበራቸው ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውንም ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።