በአዲስ አበባ በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ

ጥር 17/2014 (ዋልታ) በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን እግዱ ተነስቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሬት ነክ አገልግሎትን አግዶ መቆየቱ ይታወቃል።

ጊዜያዊ እግዱ በአሁን ወቅት ተነስቶ አገልግሎቱ ከጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በየክፍለ ከተማው እየተሰጠ እንደሚገኝ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶችም ከዚህ በታች ተጠቁመዋል፡፡

  1. ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ
  2. የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት
  • የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት
  1. የስመ ንብረት ዝውውር ስራ
  • በባንክ ሐራጅ የተሸጠ
  • በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ
  • የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት
  • በውርስ የተላለፈ ንብረት
  • በReal estates አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ
  1. ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን
  2. የንብረት ግመታ
  3. በይዞታ ይገባኛል ክርክር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት
  4. የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/
  5. በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት
  • ካሣ ክፍያ
  • ምትክ ቤት
  • ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች
  1. የቦታ ዝግጅት
  2. የወሰን ማስከበር ተግባራት
  3. በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል
  4. የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ
  5. አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
  • የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው
  • ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣
  • የReal estates ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ/