ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ከናሚቢያ አቻቸው ጋር ተወያዩ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከናሚቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኔቱምቦ ናንዲ-እንዳይትዋ ጋር ተወያዩ።
ከ40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው የመከሩት ሁለቱ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያና የናሚቢያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡