ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማት የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

ጥር 25/2014 (ዋልታ) ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማትና ኤምባሲዎች የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሜኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መካሄድ የጀመረውን 40ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደሩ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት ጉባኤው በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ ነው።

በአኅጉራዊ ሰላምና መረጋጋት፣ በኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአጀንዳ 2063 አፈጻጸም እንዲሁም በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል።

ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማትና ኤምባሲዎች የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መተላለፉን ያስታወሱት አምባሳደር ዲና በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጽሑፍ ለሰብኣዊ መብት መከበር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጧን መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነትም ተፈጸመ የተባለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት ከተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ተቋም ከኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጥምረት ማጣራቱን አስታውሰዋል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!