በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ሊኖር አንደሚገባ ተገለፀ

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ሊኖር እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመረጃ አቅርቦት የተሻለ ሥራ በመስራት ከመረጃ ሥርዓት ጋር በተገናኘ ያሉባቸውን ችግሮች ሊቀርፉ እንደሚገባ ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎቹም በተቋማቱ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን እና ተግዳሮቶችን አንስተው ውይይተ ተካሂዷል።

ከመረጃ አያያዝ ሥርዓት በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ፣ ሰላማዊ መማር ማስተማር ማስፈንና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመዋቅር ጥናት ሰነዶች ላይ ውይይት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW