ለኢድ አልፈጥር እና ኢድ አልአድሀ የዳያስፖራ የአገር ቤት ጥሪ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) ለኢድ አልፈጥር እና ኢድ አልአድሀ የዳያስፖራ የአገር ቤት ጥሪ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብት፣ ፖለቲካና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ላይ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ዳያስፖራዎች በበቃ እንዲሁም “ሆም ካሚንግ” በሚል የገና እና ጥምቀት በዓልን ወደ አገር ቤት መጥተው በተለያዩ ተግባራት ከአገራቸው ጎን መሆናቸውን እንዳሳዩ አውስተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመርኃ ግብሩ ወደ አገራቸው ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን አስፈላጊው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

መርኃግብሩ ዳያስፖራው በአገራዊ ጉዳይ እንዲሳተፍ እድል ይፈጥራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW