ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪን በመቀበል ከተለያዩ የዓለም አገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ እንግዶች የ70 በመቶ የሞባይል አገልግሎት ቅናሽ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ እስከ 70 በመቶ ቅናሽ ማድረጉንና ወደ አገራቸው ለመጡ እንግዶችም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
የተቋሙ መረጃ እንዳመለከተው አገልግሎቱን ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና በሁሉም የሽያጭ ማዕከሎች ማግኘት ይቻላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ ከተለያዩ የዓለም አገራት እንግዶች ወደ አገር ቤት በመግት ላይ ይገኛሉ፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!