ኢትዮ ቴሌኮም “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ለሚገቡ እንግዶች ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪን በመቀበል ከተለያዩ የዓለም አገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ እንግዶች የ70 በመቶ የሞባይል አገልግሎት ቅናሽ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ እስከ 70 በመቶ ቅናሽ ማድረጉንና ወደ አገራቸው ለመጡ እንግዶችም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

የተቋሙ መረጃ እንዳመለከተው አገልግሎቱን ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና በሁሉም የሽያጭ ማዕከሎች ማግኘት ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት”  ጥሪን ተከትሎ ከተለያዩ የዓለም አገራት እንግዶች ወደ አገር ቤት በመግት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!