ሚኒስትሮችን ያካተተ ልዑክ የ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገባ

ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) ዛሬ እና ነገ በሚከበረው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ላይ ለመታደም የተለያዩ ሚኒስትሮችን ያካተተ የልዑካን ቡድን ሀዋሳ ከተማ ገብቷል፡፡
ልዑኩ የፕላን እና ልማት ሚንስትር ፍፁም አሰፋን (ዶ/ር) እና የሴቶችና ሕፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡
የልዑካን ቡድን አባላቱ ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሠ መሥተዳድር በየነ ባራሳና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል አካል የሆነው የፊጣሪ በዓል በሀዋሳ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ መሆኑን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወቃል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!