የአማራ ክልል መንግሥት ሽብር በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለው አለ

ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል መንግሥት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
የአማራ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፤ እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ እኩይ አካላትን እንደማይታገሱ ተናግረዋል።
ርዕሠ መሥተዳድሩ “ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ይህ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ያሉት ርዕሠ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም አሳስበዋል።