በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የተመራ ልዑክ የወንጪ ልማት ፕሮጀክትን እየጎበኘ ነው

ግንቦት7/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የመከላከያ ሚኒስትር እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን የወንጪ ልማት ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው።
ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
ወደ ሃይቁ መዳረሻ የሚወስዱ 32 ኪሎሜትር ርዝመት ያላቸው ሦስት መንገዶች እየተገነቡ ሲሆን አፈፃፀማቸውም 58 በመቶ መድረሱ ተነግሯል።
የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ – ደንዲ ፕሮጀክት የሀገሪቱን የኢኮ ቱሪዝም ልማት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግም እምነት ተጥሎበታል።
በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የግንባታ ሥራው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጀመሩ የሚታወስ ነው።
አሳየናቸው ክፍሌ (ከወንጪ)