በደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው የደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 127 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ደንዲ ሃይቅ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጣልያኑ “ዊ ቢውልድ” ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔትሮ ሳሊኒ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የወንጪ ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት አስተባባሪና የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በቅድሚያ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቀሚነት ማረጋግጥ ስመሆኑም ተጠቁሟል።
በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የግንባታ ሥራው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መጀመሩ ይታወሳል።