በወንጀል ድርጊት የተገኙ ንብረቶችን ለማስመለስ በሚያስችሉ የትብብር ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ግንቦት 19/2014 (ዋልታ) በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ በወንጀል ድርጊት የተገኙ ንብረቶችን ለማስመለስ በሚያስችሉ የትብብር ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በወንጀል ድርጊት የተገኙ ንብረቶችን በተመለከተ የሚደረግን መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የትብብር ስልቶች ላይ ማጠኮሩ ተነግሯል፡፡

የአለም አቀፍ ተሞክሮን ማዕከል አድርጎ በተሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ በፍትህ ሚኒስቴር በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክሬተር ጄነራል ዉስጥ የሚሰሩ ዐቃቢያነ ሕግ እና ሀብት ምርመራ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

በስልጠና አጠቃላይ የሕግ ጉዳይ ትብብርን የሚመለከቱ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን የአለም ባንክ እና የዩኤንኦዲሲ (UNODC) የጋራ ፕሮጀክት ከሆነው ስታር ኢኒሼቲቭ (Star Initiative) በመጡ ባለሙያዎች ስልጠናውን ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ከመረጃ ደህንነት አገልግሎት የተጋበዙ ተወካዮችም ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ስለተቋማቸው የአሰራር ስርዓት ገለፃ ማድረጋቸውን የሚኒስቴ መረጃ ያመላክታል::